Wednesday 9 March 2011

March 8 Celebrated by the members and supporters of the EPRP in Oslo






 

1 comment:

  1. የኖቤል ሠላም ተሸላሚነት ከ አደባባይና ተጠያቂነት አያድንም !!!!

    አቶ ለማ ደስታ በአሜሪካን ድምፅ አማርኛ የኖቤል ሽልማቱን ስነ ስርዐት አስመልክቶ በ ኦስሎ ቴሌቪዥን አቢይ አህመድ ከጋዜጠኞች ጋር እንደማይገናኝ መገለፁን ለማስተባበል ያደረገዉን ጥረት ለኢትዮጵያ አድማጮቹ ከዶክተር ሰለሞን ጋር በመሆን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ኖርዌይ "ተወካዮች" ሊባል በሚችል አቀራረብ።

    ዶክተር ሰለሞንም ሽልማቱ ተገቢ መሆኑን ደግፎ የራሱን ቤተሰብ በምሳሌ በማቅረብ የዉይይቱን ጊዜ በመሻማት ወደ ሽልማት ይገባል አይገባም በመዉሰድ ጥያቄው ዐቢይ ለምን ጋዜጠኛ ፈራ የሚለዉን ክርክር ጊዜ ያለአግባብ ተጠቅምዋል።

    ሽልማቱ ኖቤል ኮሚቴዉ እንደጠበቀው በኢትዮጵያና ኤርትራም ግንኙነት ያመጣው መሰረታዊ ለውጥ የለም ኢትዮጵያ ውስጥ የዘርና ሀይማኖት ጥቃት እየባሰ ነው ብሎ ከአቶ ለማ ጋር በ ኦስሎ ቴሌቪዥን የተከራከረውን የ ኖርዌይ ፕሮፌሰር ጨለምተኛ ተብሎ ዶክተር ሰለሞን ክስ መሰረተበት ሰውየው በሌለበት።

    አቶ ለማ ደስታ ጠቅላይ ምኒስትሩ ስራ ስለሚበዛበት ጋዜጠኛ ባያናግር አይገርምም ምክንያቱም ኦባማ የዛሬ አስር ዐመት ሁለት ጋዜጠኛ ነበር ያነጋገረው በስርዐቱም በሙሉ ኦባማ አልተካፈለም የሚለው የ PR ስራ ከብሌን ስዩም ከሰማነው ተጨማሪ ሊባል ይችላል።

    የ ዐለም ዐቀፍ ዜና ዘጋቢዎች ኦባማና ዐቢይ ሽልማቱ በችኮላ አገኙ ተብለው "የሚከሰሱ" በመሆናቸው ጋዜጠኛ መፍራታቸው እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎች ለመሸሽ ሲሆን ዐቢይ አህመድ ከኦባማ የሚለይበት ዋናው የኢትዮጵያ የዉስ ጥ ችግር ለማ ደስታም ሆነ ዶክተር ሰለሞን ሊደብቁ የፈለጉት ጉዳይ ዐቢይ አህመድ ከ ሜይማር መሪ ሳን ሱሲንግ ካይ የሚመሳሰልበት ጉዳይ እንጅ ከ ኦባማ ጋር የሚያመሳስለው ብቻ አለመሆኑ ግልፅነው።

    ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አህመድ ኖቤል ሽልማትና የ አሰጣጡ ስነ ስርዐት ሲነሳ ኦባማናሳን ሱን መነሳታቸው ግድ ይሆናል መቸም ጊዜ።

    ዋናው የዐቢይ አህመድ ጋዜጠኞች ሽሽት ወይም ፍርሀት የኢትዮጵያ ሁኔታ በኖቤል ሽማልቱ ማግስት በአፋር ህፃናት ሴቶች አረጋውያን ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ና ባለፈው ወር በኦሮሞ ክልል ከ 86 በላይ ንፁሀን ዘግናኝ የጎሳ ግድያ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ ሰሞኑን በፈረንሳይ ቤልጄየም ጀርመን ስዊድን የተደረገው የ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን አማኞች የተቃውሞ ሰልፎቾ ጠቅላይ ምኒስትሩ ግጭት ብለው ለተናገሩት የሚመራው መንግሥትን ተጠያቂነት ላለመቀበል የተደረገ ሽሽት መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። በ ኦስሎ ኢትዮጵያውያንም የተቃዉሞ ሰልፍ ዝግጅትንም መፍራት ሌላዉ ምክንያት ይሆናል።

    አቶ ለማ ደስታ የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት በ ኦስሎ ሀላፌ ም ሆነ ዶክተር ሰለሞን የሰጡት አስተያየት ከራስ ፍላጎት የመነጨ ሲሆን ቪኦኤ አማርኛ ዘጋቢዉም እስክንድር ፍሬውም የተለየ ሀሳብ ያላቸውና ሠላማዊ ሰልፍ በማድረግ የዐቢይ አስተዳደርን ተጠያቂነት ለማሳወቅ ካሉት ወገኖችእንግዳ አለማቅረቡ ሚዛን የጎደለው ዘገባ አድርጎታል።

    በተመሳሳይ ቀን በ ሄግ ኒዘርላንድ የኖቤል ሠላም ተሸላሚዋ ሳን ሱን ኬይ በአለም ዐቀፍ ፍርድ ቤት መንግስትዋ በሪሂንጃ መስሊሞች ላይ የፈፀመውን ዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ለመከላከል ትሄዳለች። መጠየቅ የጊዜ ጉዳይ ነው አይቀርም የኖቤል ተሸላሚ ሲኮን እንዲያውም መደበቅ አይቻልም።

    ReplyDelete